Job Type:Health Facility / Hospital

 

Fields of Education: በሳይኮሎጂ ወይም በሶሾ ሎጂ ወይም በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ

 

Organization: የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

 

Salary : 6488.00

 

Posted:2016-06-23

 

Application Dead line:2016-07-06

 



የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከዚህ በታች በተመለከቱት ክፍት የስራ መደቦች ላይ የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ አመላካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የስራ መደብ መጠሪያ

የስራ  ደረጃ

መነሻ  ደመወዝ ወዝ

ብዛት

ተፈላጊ ችሎታ

 የስራ ልምድ

1

የጤና መረጃ አማካሪ

ኘሳ 5/1

6488.00

7

በሳይኮሎጂ ወይም በሶሾ ሎጂ ወይም በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ ወይም በቢኤስ ሲነር ሲንግል ወይም በህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ወይም በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ የተመረቀ/የተመረቀች

ለመጀመሪያ ዲግሪ 8 አመት የሰራ ልምድ፣

ለማስተማር ዲግሪ 6 አመት የስራ ልምድ

 
ማሳሰቢያ፡-

952 ነፃ የጤና የስልክ ጥሪ ማዕከል ሲሆን ቀደም ሲል ለበርካታ ዓመታት በኤች.አይ.ቪ፣ በአባላዘር በሽታ እና በቲቢ ላይ ጥራቱን ሚስጥራዊቱን የተጠበቀ  የጤና መረጃ አገልግሎት፣ የምክር አገልግሎት እንዲሁም የሪፈራል አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ማዕከሉ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ስር እንዲሆን ስለተደረገ ከዚህ በፊት ሲሰጣቸው ከነበረው ቸገልግሎት በተጨማሪ ቅድሚያ በተሰጣቸው የጤና ችግሮች ላይ ለመስራት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በዚህ የቅጥር ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሱት የስራ መደቦች ተመዝግበው የውድድሩ ቸሸናፊ የሚሆኑ ባለሙያዎች የሚያከናውኑት ስራ በስልክ የጤና መረጃ፣ የምክርና የሪፈራል አገልግሎት መስጠት መሆኑን ተገንዝበው በተጠቀሱት የተፈላጊ ችሎታ መሰረት ተመዝግባችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

 

  1. የቅጥር ሁኔታ፡- በቋሚነት ነው፣

  2. ሴት አመልካቶች ይበረታታሉ፣

  3. የስራ ቋንቋው፡-  አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ትግርኛ፣ አፋርኛ፣ ሲዳምኛ፣ ጉራግኛ፣ ሀዲይኛ፣ከምባትኛ፣ወላይትኛ፣ስልጥኛ፣ ሱማልኛ፣

  4. በተጠቀሱት የስራ  መደቦች ላይ የምትወዳደር መመዝገብ የምትችሉት ወቅታዊ የሙያ ምዝገባ ፈቃድ ስታቀርቡ ነው፣

  5. በጤና ሙያ በዲፕሎማ ከተሰጠ አገልግሎት ውስጥ ከፍተኛው የሚያዘው የአራት ዓመት አገልግሎት ብቻ ነው፣

  6. በተፈላጊ ችሎታው ከተገለፀው የትምህርትና የስራ ልምድ በላይ ማስረጃ ያላቸው አመልካቾች መወዳደር ይችላሉ፣

  7. አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ጠዋት ከ 2፡30-6፡30 ሰዓት ፣ ከሰዓት በኋላ ከ 7፡30-11፡30 ሰዓት የትምህርትና የስራ ልምድ ማሰረጃዎቻችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ የመጀመሪያ  ሕንፃ ሰው ሀብት ልማትና አስ/ዳይሬክቶሬት ቀርባችሁ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ የሚቀርበው የስራ ልምድ ማስረጃ  ወቅታዊ ያልተደለዘ፣ የስራውን ዓይነት፣ የደመወዝ ልክ፣ ከመቼ እስከ መቼ እንደሰራ ጊዜውን ለይቶ የሚገልጽ  የአሰሪውን ሙሉ ስም ፊርማና የስራ ደረጃ ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከግል ድርጅት የሚቀርበው ማስረጃ ከፍ ብሎ ከተጠቀሰው በተጨማሪ ተገቢው  የስራ ግብር ስለመከፈሉ የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡ የክልል አመልካቶች በግንባር፣ በወኪል/ በፖስታ በፋክስና በሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የስራ መጠየቂያ  ቅጽ ከሌላ ግን የማስረጃዎቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከግል ሁኔታ መግለጫ/CV/ ጋር በማያያዝ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 1234 መላክ ይችላሉ፡፡

 

አድራሻችን፡ በልደታ ክፍለ ከተማ 07/14

የኢትዮጵያ   ጎማ ቁጠባ አጠገብ

ስልክ ቁጥር 0115-159869፣0911-417852፣0911-678454

ፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

 

 

 

Please Click here
to move back to job lists