Quick Links
- ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የክብር አምባሳደር ሆኖ ተሰየመ:
- ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ በአዲሱ ዓመት የማስትሬት ፕሮግራሞችን ሊያስተዋውቅ ነው
- Economic Activities in Hawassa
- ንግድ ባንክ የበጀት ዓመቱ ክንውን አመርቂ መሆኑን ገለጸ
- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በዓመቱ ውስጥ ግማሽ ቢሊየን ብር ማትረፉን ገለፀ
- የሀዋሳ ዪኒቨርስቲ ምሩቃን ሀገር አቀፍ ፈጠራ ተሸላሚዎች
- National Technology Roadmap
- አዲሷ አለም አቀፍ የቡና ቢዝነስ ተፅዕኖ ፈጣሪ
- የ2008 , የ300 ሺሕ ብር ፈጣሪዎች
- ከመስከረም 2009 ጀምሮ በ7.5 ሚሊየን ዶላር ሰብል የማዳቀል ስራ ሊጀመር ነው
- 400 ሺሕ ሰዎችን ለመቅጠር የሚያስችሉ ፓርኮች፣ በአማራ፣ በአሮሚያ፣ በደቡብና በትግራይ ክልሎች ሊገነቡ ነው
- የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 7ኛ የሆነው የበንሳ ዳዬ ካምፓስ ግንባታውን ጀመረ
- የአተት በሽታን ለመከላከል ትኩረት ሚሹ ጉዳዮች
- የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ወደ ቀድሞ ቦታው ሊመለስ ነው
- አዲሱ የፌስቡክ የአይነስውራን ቴክኖሎጂ
- Tourist Facilities in Hawassa
- Ethiopian Airlines Career/Training Opportunities
- Hospitality and Hotels Ranking in Ethiopia
- Blessed Coffee Wins Start Up Africa Entrepreneurship
- Hawassa 2014 Livestock Investment Forum
- Hawassa City Background
- Amora Gedel Fish Market
- Experience Hawassa
- Foundation of Hawassa City
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 7ኛ የሆነው የበንሳ ዳዬ ካምፓስ ግንባታውን ጀመረ
በደቡብ ክልላዊ መንግሥት ከሐዋሳ ከተማ በ125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዳዬ ከተማ በ200 ሔክታር ቦታ ላይ፣ በ650 ሚሊዮን ብር ወጪ የዩኒቨርሲቲ ግንባታ ሐምሌ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ተጀመረ፡፡ ዩኒቨርሲቲውን ኃላፊነት ወስዶ የሚያስገነባው የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ መሆኑንና አዲስ የሚገነባው ዩኒቨርሲቲ ስያሜ ‹‹ዳዬ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ›› እንደሚባል፣ ግንባታውን ያስጀመሩት የዳዬ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ ገልጸዋል፡፡
ከዓመት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ማለትም አካባቢውን ማፅዳትና ለነዋሪ አርሶ አደሮች ካሳ በመክፈልና ምትክ ቦታ በመስጠት ቢዘገይም በዚህ ወቅት መጀመሩ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡ በ200 ሔክታር ቦታ ላይ የሚነሱት 488 አርሶ አደሮች ሲሆኑ፣ ለ114 ተነሺዎች ሙሉ በሙሉ የካሳ ክፍያ መፈጸሙንና ለቀሪዎቹ በመክፈል ጎን ለጎን የግንባታ ሥራ እንደሚከናወንም ተናግረዋል፡፡ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በተጨማሪ፣ ለከተማዋ ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከልማቱ ጎን እንዲቆምም ከንቲባው አሳስበዋል፡፡ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ650 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት በመፈራረም ወደ ተግባር ግንባታ የገባው ከተክለብርሃን አምባዬ ኮርፖሬት ግሩፕ ጋር ነው፡፡ ግንባታውን በኃላፊነት ከሚያስፈጽመው ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዮሴፍ ማሞ ጋር በመሆን ያስጀመሩት፣ የኮርፖሬት ግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፉ አምባዬ ናቸው፡፡
በተጠናቀቀው ዓመት የይርጋለም ካምፓስን አጠናቀው ማስረከባቸውን የገለጹት ሥራ አስፈጻሚው፣ የጀመሩት የዳዬ ዩኒቨርሲቲንም ለ2010 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ለማድረስ ጠንክረው እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡ ኮርፖሬት ግሩፑ ወደ ግንባታው ቦታ ይዞ የሚቀርበው ከፍተኛ ማሽኖችንና ከፍተኛ ባለሙያዎችን ብቻ መሆኑን የገለጹት አቶ ሰይፉ፣ ሌላውን የሰው ኃይል የሚቀጥሩት በዳዬ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ወጣቶቹን በማሠልጠን ወደ ሥራው እንዲገቡ ስለሚያደርጉ ተደራራቢ ጥቅም እንደሚያስገኙም አክለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ የሰጠው ጊዜ ሁለት ዓመት ቢሆንም፣ ኮርፖሬት ግሩፑ ግን በአንድ ዓመት ከሦስት ወራት በማጠናቀቅ እንደሚያስረክብም አቶ ሰይፉ ቃል ገብተዋል፡፡ የክልሉን ልማት ከማገዝ አንፃር፣ ‹‹አንድ አንገብጋቢ ነው የምትሉትን የልማት ጥያቄ አቅርቡልንና አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን፤›› ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የማታና የድኅረ ምረቃን ሳይጨምር 20,000 መደበኛ ተማሪዎችን እንደሚያስተናግድም ተጠቁሟል፡፡
Source: The Ethiopian Reporter, ረቡዕ ሐምሌ 27 ቀን 2008 , hu.edu.et