እንዲሁ የምንጥለው የበቆሎ እሸት ሀር በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ያውቃ?

እንዲሁ የምንጥለው የበቆሎ እሸት ሀር በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ያውቃሉ?

 

እንዲሁ የምንጥለው የበቆሎ እሸት ሀር በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ያውቃሉ?

 

 

በቆሎ እሸት ስንፈለቅቅ የምናገኘው ሀር መሳይ ነገር ጥቅም ይኑረው አይኑረው አስበነው የምናውቅ አይመስልም።

እሸቱን ለመጥበስ ወይም ለመቀቀል ነው እንጂ ለሽፋኑም ሆነ እሸቱን ሸፍነውት ለነበሩት ፀጉር መሳይ ፋይበሮች ትኩረት አንሰጣቸውም።

ምናልባትም ሽፋኑን የተጠበሰ አልያም የተቀቀለ የበቆሎ እሸትን ለመያዝ ልንጠቀምበት እንችላለን።

ሀር መሳዮቹን ነገሮች ግን ከቁብ የማንቆጥራቸው ብዙዎች ነን። ይሁን እንጂ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።

የበቆሎ እሸት ሀር የልብ ህመም ለመከላከል እና ጥቅም የሌለው የኮሊስትሮል መጠንን ለመቀነስ የሚረዱ ስቲግማስቴሮል እና ሲቶስቴሮል የተሰኙ ንጥረ ነገሮች አሉት።

የአፍ እና ቆዳ ችግሮችን ለማስወገድ የሚረዱ እና በሰውነት ውስጥ የግሉኮስ መጠንን የሚቆጣጠሩ አሲዶችንም ይዟል።

 

የበቆሎ እሸት ሀር ጥቅሞች፦

የኩላሊት ጠጠርን ይከላከላል

የበቆሎ እሸት ሀር ለዘመናት የኩላሊት ጠጠርን አስቀድሞ ለመከላከል ጥቅም ላይ ውሏል።

የተስተካከለ የሽንት አወጋገድ እንዲኖር እና በመገጣጠሚያዎች አካባቢ የክሪስታል (ቅንጣቶች) ክምችትን ለመቀነስም ይረዳል።

ለኩላሊት ጠጠር ቅድመ መከላከል እንጂ በህመሙ ከተጠቃን በኋላ ግን መፍትሄ አይሆንም።

የደም መርጋትን ለመቀነስ ይረዳል

የበቆሎ እሸት ሀር በቫይታሚን ኬ የበለፀገ በመሆኑ የደም መርጋትን ለመከላከል እና በአደጋ ወቅት ከፍተኛ ደም እንዳይፈሰን ይጠቅማል።

በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይቆጣጠራል

በጣፊያ ላይ የተጎዱ ህዋሳት መልሰው እንዲያገግሙ የኢንሱሊን መጠኑን ከማሳደጉም በላይ የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ይቆጣጠራል።

የኮሊስትሮልን መጠን ለመቆጣጠር ይረዳል

ከፍተኛ የሆነ ለሰውነት የማያሰፈልግ ኮሊስትሮል ለልብ ህመም ያጋልጣል፤ ይሁን እንጂ የበቆሎ እሸት ሀርን በመጠቀም የኮሊስትሮል መጠንን መቆጣጠር ይቻላል።

የበቆሎ ሀርን በዋናነት የምንጠቀመው በሻይ መልክ በማዘጋጀት ነው።

 

አዘገጃጀት

አንድ ማንኪያ የሚሆን የተፈጨ የበቆሎ እሸት ሀር በአንድ ኩባያ ውሃ ማፍላት

ከፈላ በኋላ ማፍያውን ከድነን ለ15 ወይም 20 ደቂቃ እንዲቀዘቅዝ ማድረግ

ከቀዘቀዘ በኋላ ካስፈለገን 1 ማንኪያ ማር ጨምረን መጠጣት እንችላለን።

የምንጠጣው የበቆሎ እሸት ሀር ሻይ ካለንበት የጤና ሁኔታ እና የሰውነታችን ክብደት አንፃር ሊለያይ ይችላል

ብዙ ጊዜ ለወጣቶች የሚከረው 1 ስኒ ሻይ ሆኖ በቀን ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ እንዲወሰድ ነው።

ባለሙያዎች የበቆሎ ሀር ሻይን ከመተኛታችን በፊት መውሰድ እንደሌለብን ይመክራሉ።

ማንም ሰው ይህን ሻይ የተለያዩ ህመሞችን ለማስታገስ ከመውሰዱ በፊት ሀኪሙን እንዲያማክርም ነው የሚያሳስቡት።

ማሳሰቢያ፦ የበቆሎ እሸት ሀር ሻይን ነፍሰጡሮች ባይጠጡ ይመከራል።

 

ምንጭ፦ www.realnaturalcare.com/ እና www.stylecraze.com/