የጉበት ላይ ስብነት (ፋቲ ሊቨር)

የጉበት ላይ ስብነት (ፋቲ ሊቨር)

 

 

17754258 - fatty liver disease

 

ከአልኮልነት ጋር ያልተያያዘ የጉበት ላይ ስብ ማለት በጣም ትንሽ ወይም ምንም አይነት አልኮሆል ሳይጠቀሙ/ሳይጠጡ በጉበት ላይ የስብ መጠራቀም ችግር በሚከሰትበት ወቅት ነዉ፡፡

 

የህመሙ ምልክቶች

ችግሩ ምንም የህመም ምልክት ላያሳይ ይችላል፡፡ ነገር ግን የህመም ምልክቶች ከታዩ የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡

የሰዉነት ድካም

በቀኝ የላይኛዉ የሆድ ክፍል ህመም መሰማት

የክብደት መቀነስ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

 

የህመሙ ምክንያቶች

የጉበት ላይ ስብ መጠራቀም የሚከሰተዉ ጉበት ስብን ለመሰባበር በሚየደርገዉ ሂደት ላይ ችግር ሲገጥመዉ ሲሆን ይህ ክስተት ስብ በጉበት ላይ እንዲጠራቀም ያደርገዋል፡፡

 

ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች

 

የሰዉነት የኮለስትሮል መጨመር

በደም ዉስጥ ያለዉ የትራይግላይስራድ ስብ መጠን መጨመር

ሜታቦሊክ ሲንድረም

ዉፍረት

ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም የሚባለዉ የጤና ችግር ሲኖር

ስሊፕ አፕኒያ( ከእንቅልፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ችግሮች)

የስኳር ህመም ሲኖር

የታይሮይድ ችግር ሲኖርና የመሳሰሉት ናቸዉ፡

ምንጭ፡-hellodoctorethiopia