የምናነጥሰዉ የመተንፈሻ ስርአታችን በየጊዜዉ መጠገንና መልሶ ማስታከከል

 

ጥቂት ነጥቦች ስለ ማስነጠስ

 

Image result for ማስነጠስ

 

. የምናነጥሰዉ የመተንፈሻ ስርአታችን በየጊዜዉ መጠገንና መልሶ ማስታከከል (Reset) ማድረግ ስላለበት ነዉ፡፡

. በተደጋጋሚ ጊዜ የምናስነጥስ ከሆነ ምክንያቱ በአነጣጠሣችን ጋር የተያያዘ ነዉ፡፡ የምናነጥሰዉ በአፍንጫችን አካባቢ የሚቆጠቁጠንን ስሜት  ለማስወገድ ጭምር ነዉ፡፡ ይህን ሰሜት ለማበረር ሁለትም ሶስትም አራትም ጊዜ ማነጠስ ሊኖርብን ይችላል፡፡

. ስናነጥስ ልባችን ቀጥ ትላለች የሚለዉ ነገር መሰረተ ቢስ ነዉ፡፡ በተለይ በኃይል ካነጠስን ልባችን ምቷን ያቆመች ሊመስለን ቢችልም እሷ ግን አትቆምም፡፡

. የአፍንጫዎ የውስጥ አካል መጠን የማነጠስዎን የድምጽ መጠን ይወሰነዋል፡፡ በምናነጥስበት ወቅት አየር በአፍንጫዎቻችን ውስጥ በሰዓት 160 ኪሎ ሜትር በሆነ ፍጥነት ይወረዉራል፡፡

.  በምናስነጥስበት ወቅት ከአፍንጫችን የሚወጣዉ ንፍጥ (Mucus)ነጣ ያለ ቀለም እንዲኖረዉ ይጠበቃል፡፡ ይሁ እንጂ አረንጓዴ ፤ቢጫ ወይም ቡናማ ቀለም ያለዉ ልናይ እንችላለን በተደጋጋሚ እንደታየዉ ንፍጡ ከነዚህ ቀለማት አንዱን ከመሰለ የኢንፌክሽን ምልክት እንደሆነ ይታመናል፡፡ ህክምና ለማግኘትም ሀኪሞን እንዲጎበኙም ይመከራል፡፡

. ዐይናችን ሳንጨፍን ማነጠስ አንችልም፡፡ አንዳንዶች ስናፏጭ እንደበላ ሰዉ አናታቸዉ ድረስ ሰርስሮ በሃይለኛ ድምጽ የሚወጣ ማነጠስ ያላቸዉ ያህል ቀጭን ፉጨት የመሰለ ድምጽ የሚያሰሙም አሉ፡፡

ምንጭ፡- አዲስ ጉዳይ ቁ.207