በጆሮ ላይ የሚከሰተውን ችግር ለመግታት ለጆሮ የሚደረጉ እንክብካቤዎች ከ?

በጆሮ ላይ የሚከሰተውን ችግር ለመግታት ለጆሮ የሚደረጉ እንክብካቤዎች ከፍተኛ ፋይዳ አላቸው፤

 

Image result for ጆሮ

 

እጅግ በጣም ጥንቃቄ ከሚያስፈልጋቸው የሰውነት ክፍሎች አንዱ ጆሮ ነው። «ለምን?» ቢባል በቀላሉ ለህመም የመዳረግ ዕድሉ የሰፋ ስለሆነ ነው። በተለይ በዚህ የሰውነት ክፍል ላይ ከሚከሰቱና ጠንከር የሚሉት ህመሞች የጆሮ ውስጥ መመርቀዝ (ኢንፌክሽን) ነው። ይህ ችግር ከትንሽ ቁስለት በመነሳት ከፍ ወዳለ የጤና እክል የሚደያርስ ነው።

ይህ ችግር ከቀላል ጀምሮ ከፍ ወዳለ ደረጃ የሚሄድ እንደመሆኑ መጠን ከፍተኛ

ጥንቃቄ ይጠይቃል፤ ጆሮ ለማጽዳት የሚደረግ ጥንቃቄ አልባ ሂደት፣ የምግብ አለርጂ፣ የአየር ንብረት፣ ከልክ በላይ የአልኮል ሱሰኝነት፣ አፈጣጠር፤ የተመጣጠነ ንጥረ ምግብ እጥረት፣ ሰውነት ላይ የሚከሰት ውስጣዊ ጉዳት እና የመሳሰሉት የዚህ ህመም ችግር መንስኤዎች ናቸው። በዚህ ህመም የተጠቃ ሰው ደግሞ የጆሮ ውስጥ ህመም፣ የእንቅልፍ እጦት፣ ራስ ምታት፣ በደንብ አጥርቶ መስማት አመለቻል፣ ከፍተኛ ትኩሳት፣ በጆሮ ፈሳሽ መውጣት፣ ማስመለስ እና አጣዳፊ ተቅማጥ ሊከሰትበት ይችላል። በቀላሉ ትንሽ ነጥብ መስሎ የሚጀምረው የጆሮ ቁስለት ቀስ በቀስ እየሰፋ በመሄድ ከፍ ያለ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት ህክምና ማግኘት እና መፍትሔ መስጠቱ የተሻለ ነው።

ከተለያዩ ድረ ገጾች ያገኘነውመረጃ እንዲሚ ያመለክተው የጆሮ ውስጥ ህመምን ለማከም ደግሞ ወደ ሐኪም ቤት ከመሄድ ባለፈ፤ ቤት ውስጥ በቀላሉ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ማከም ይቻላል። ለዚህም ጨው፣ ቀይ እና ነጭ ሽንኩርት፣ የወይራ ዘይት፣ ለብ ያለ ውሃ እና የማንጎ ቅጠልን በመጠቀም ማከም እና ፈውስ ማግኘት ይቻላል። አንድ ስኒ ጨውን በመጥበሻ ላይ አድርጎ እያገላበጡ ለብ ማድረግ እና ከእሳት ላይ አውርዶ በጨርቅ መጠቅለል። ከዚያም ሞቅ ያለው ጨው እንዳይበተን ጫፉን በመቋጠር የተጎዳው ጆሮ አካባቢ ከ5 እስከ 10 ደቂቃ ማቆየት። ይህንንም እንደ አስፈላጊነቱ በየቀኑ መደጋገም።

ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርትን ከሁለት የሻይ ማንኪያ ሰሊጥ ጋር ቀላቅሎ ማፍላት። ከዚያም ከሁለት እስከ አራት ጠብታ የውህዱን ፈሳሽ የተጎዳው የጆሮ ክፍል ላይ ማፍሰስ ወይም ደግሞ ሦስት ራስ ነጭ ሽንኩርትን በጨው ማፍላት እና አቀዝቅዞ በጨርቅ በመጠቅለል በጥቂት በጥቂቱ እያደረጉ ለተወሰነ ጊዜ በተጎዳው የጆሮ ክፍል ላይ ማስቀመጥ መፍትሔ ነው።

አንድ ነጠላ ፍሬ ነጭ ሽንኩርትን በመላጥ በተጎዳው የጆሮ ክፍል ውስጥ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ማስቀመጥ። ለጆሮ ጠብታ የሚጠቀሙትን ያህል ጥቂት የወይራ ዘይት ለብ ማድረግ፤ ከዚያም ጥቂት አውርዶ ማቆየት፤ በመቀጠል ይህን ጠብታ በተጎዳው የጆሮ ክፍል ላይ መጥኖ ማድረግ መፍትሔ ነው። ጠብታው ግን በጣም ዘልቆ እንዲገባ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ጠብታ ካደረጉ በኋላ ወደ አንድ ጎን አለማጋደልና ቀጥ ብለው ለተወሰነ ጊዜ መቆየት፤ ከቆይታ በኋላ በጠብታው ታግዞ የሚወጣውን ቆሻሻም በንጹህ ጥጥ ቀስ አድርጎ መጥረግ። በጥቂቱ ለብ ያለ ውሃን በጠርሙስ በማድረግ በተጎዳው የጆሮ ክፍል ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች መያዝ ይገባል።

ይህንን ለብ ያለ ውሃ በተጎዳው ክፍል ላይ ማንከባለልም ተገቢ ነው። ነገር ግን ውሃው በጣም መሞቅ የለበትም። ቆይታውም የተወሰነ ጊዜ መሆን አለበት።

ሌላው መፍትሔ አንድ ከፍ ያለ ቀይ ሽንኩርትን ልጦ እሳት ላይ በመጣድ ለሁለት ደቂቃ ማፍላት። ከዚያም የፈላውን ቀይ ሽንኩርት ውህድ ከእሳት አውርዶ ማቀዝቀዝ እና እስከ 3 የሻይ ማንኪያ ጠብታን በተጎዳው ጆሮ ውስጥ ማፍሰስ። ይህንን ለተወሰኑ ደቂቃዎች ካቆዩት በኋላ ፈሳሹን ባስገቡበት አንገትዎ በማጋደል ፈሳሹ እንዲወጣ ማድረግ። ወይም ደግሞ አንድ ተለቅ ያለ ሽንኩርትን በጥቂቱ በመቆራረጥ በተጎዳው የጆሮ ክፍል ውስጥ በማስገባት እስከ 5 ደቂቃዎች ያክል ካቆዩ በኋላ በጥንቃቄ ማስወገድ።

ሦስት የማንጎ ቅጠሎችን ቆርጦ ማጽዳት መቀነጣጠስ፤ ከዚያም ቅጠሎቹ እንዳይቃጠሉ ጥቂት ውሃ ጠብ አድርጎ ማፍላት። ፈልቶ የቀዘቀዘውን የቅጠል ፈሳሽ እስከ 3 ጠብታ በተጎዳው የጆሮ ክፍል ውስጥ ማፍሰስ እና ለተወሰኑ ደቂቃዎች ማቆየት። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ሲያደርጉ ጆሮ ውስጥ የተከማቹ ቆሻሻዎችን ማስወገድ እና ማጽዳት ያስችልዎታል። ከዚህ ባለፈም የጆሮ ቁስለትን ማከም፣ እብጠቱን ማጉደልና መመርቀዙን ማስወገድ ያስችልዎታል። ይህን ህክምና ሲያደርጉ ግን በጣም የሞቀ ውሃም ሆነ የውህዶችን ፈሳሽ አብዝቶ አለመጠቀም፤ ውህዱ ወደ ጆሮ ውስጥ በጣም ዘልቆ እንዲገባ መጠንቀቅም ያስፈልጋል።

 

ምንጭ፡- ሪፖርተር ጋዜጣ