አስደናቂ ጤና ነክ 40 እውነታዎች

አስደናቂ ጤና ነክ 40 እውነታዎች

 

1. ግማሽ ሊትር ደም በመለገስ ብቻ የአራት ሰው ህይወት ሊታደጉ ይችላሉ፡፡

2. ሴቶች በአማካይ 4.5 ሊትር ደም ሰውነታቸው ውስጥ ሲኖር ወንዶች በአማካኝ 5.6 ሊትር ደም ውስጣቸው ይኖራ

ል፡፡

3. ሁሉም ህፃናቶች ሲወለዱ ቀለማትን መለየት አይችሉም፡፡

4. ስታለቅሱ አፍንጫችሁ ፈሳሽ የሚያበዛው እንባችሁ ከአይናችሁ ወደ አፍንጫችሁ ስለሚሄድ ነው፡፡

5. አይናችሁን ከፍታችሁ ማስነጠስ በፍፁም አትችሉም፡፡

6. ወንዶች በአማካይ ከዕድሜያቸው ላይ አምስት ወር ያህል ፂማቸውን በመላጨት ያጠፋሉ፡፡

7. ፀጉር እና ጥፍር የተሰሩት ከተመሳሳይ ንጥረ ነገር ነው፡፡

8. ከ90% በላይ የሚሆኑ በሽታዎች የሚፈጠሩት እና የሚባባሱት በውጥረት ምክንያት ነው፡፡

9. ሴት ልጅ በጡት ካንሰር የመያዝ እድሏ አልኮል አለልክ በመጠጣት ይባባሳል፡፡

10. በየዓመቱ አሜሪካን ሀገር ከውፍረት ጋር የተያያዘ 300.000 ሞት ይከሰታል፡፡

11. የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች 6.5 ዓመት ቀድመው ይሞታሉ፡፡ በቀን በአማካይ አንድ ፓኬት ሲጋራ የሚያጨስ ሰው በየአስር ዓመት ልዩነት ሁለት ጥርስ ያጣል፡፡

12. ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ሙዚቃ ማዳመጥ ለምግብ ለመፈጨት ሂደት ጠቃሚ ነው፡፡

13. የእንቅልፍ እጦት በሽታ የመከላከል አቅምን ይቀንሳል፡፡

14. ከአርባ ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን የከፋ የአፍ ጠረን ችግር አለባቸው፡፡

15. ካርቦን ሞኖክሳይድ ከአስራ አምስት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሰው ሊገድል ይችላል፡፡

16. በየዕለቱ ሰውነታችን ሁለት ሊትር ያህል ሀይድሮ ክሎሪክ አሲድ ያመነጫል፡፡

17. ሳቅ ፍቱን የህመም ማስታገሻ (pain killer) እንደሆነ የህክምና ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡

18. የእርጉዝ ጥርስ ጤንነት ያልተወለደውን ልጅ ጤንነት ሊወስን ይችላል፡፡

19. ሴት ልጅ እርግዝና ውስጥ ስትሆን ሁሉም የስሜት ህዋሶቿ ከልክ በላይ ይነቃቃሉ፡፡

20. መሳሳም የጥርስ መበስበስን ይከላከላል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው መሳሳም የሚፈጥረው ምራቅ የጥርስን እርጥበት መጠ

ን ስለሚያስጠብቅ ነው፡፡

21. ጡት ጠብተው ያደጉ ልጆች ጡት ሳይጠቡ ከማያድጉ ልጆ ይልቅ ሸንቃጣ ናቸው፡፡

22. ነጣ ያለ ቆዳ ያላቸው ሰዎች ጠቆር ያለ ቆዳ ካላቸው የበለጠ ቆዳቸው ቶሎ ይጨማደዳል፡፡

23. አለርጂ ያለባቸው ሰዎች በመሳቅ የአለርጂ መጠናቸውን መቀነስ ይችላሉ፡፡

24. የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች የበለጠ ቆዳቸው ይጨማደዳል፡፡

25. ጡት ጠብቀው ያደጉ ልጆች ጡት ጠብተው ካላደጉ ልጆች የበለጠ IQ ሊኖራቸው ይችላል፡፡

26. በወር ሶስት ጊዜ ቸኮሌት መብላት ከልክ በላይ ከሚበሉና እንደውም ከማይበሉ ሰዎች የበለጠ ረጅም ጊዜ ለመኖር

ያስችላል፡፡

27. በአማካይ አንድ ሰው በአንድ ሌሊት ውስጥ 7 ህልም ይመለከታል፡፡

28. አንድ ሰው በዕድሜ ዘመኑ በአማካይ የምድርን ዙሪያ ሁለት እጥፍ ያህል ይጓዛል፡፡

29. አንድ ሰው በአማካይ በቀን 15 ጊዜ ያህል ይስቃል፡፡

30. የአንድ አማካይ ሰው መዝገበ ቃላት ብዛት ከ5,000 እስከ 6,000 ነው፡፡

31. የዓለማችን 10% ያህል ህዝብ ግራኝ ነው፡፡

32. የሰው ልጅ አንድ ነጠላ ፀጉር ሶስት ኪሎ ግራም ክብደት መሸከም ይችላል፡፡

33. ፈገግ ከማለት ይልቅ ኮስተር ማለት ብዙ ጡንቻ ይጠይቃል፡፡

34. 1/3 የካንሰር ህመምን መከላከል ይቻላል፡፡

35. በምታስነጥሱበት ወቅት ሁሉም የሰውነታችሁ ስራ ይቆማል ልባችሁን ጨምሮ፡፡

36. የሰው ልጅ ጉበት ከአምስት መቶ በላይ ተግባሮችን ያከናውናል፡፡

37. የልባችሁ መጠን የአንድ እጅ ጭብጣችሁን ያህል ነው፡፡

38. በሳምንት ለሶስት እና አራት ሰዓት ያህል ፈጣን የእግር ጉዞ ማድረግ በልብ ህመም የመያዝ ዕድልን በ65% ይቀንሳል፡፡

39. ከመሳሳም የበለጠ በመጨባበጥ ከሰው ወደ ሰው ሊተላለፉ የሚችሉ ብዙ ጀርሞች አሉ፡፡

40. እንቅልፍ ከምግብ የበለጠ አስፈላጊ ነው፡፡ አንድ ሰው በእንቅልፍ እጦት ከምግብ እጦት አስቀድሞ ሊሞት ይችላል፡፡

 

Source: Zehabesha