ሰስ በተራራማ አካባቢ የሚኖር እንስሳ ነው፡፡

ሰስ

 

 

 

ሰስ በተራራማ አካባቢ የሚኖር እንስሳ ነው፡፡ ከአጥቢ እንስሳ የሚመደቡ ሲሆን፣ ምግባቸውም አበባ፣ ሰፋፊ ቀጠል፣ ፍራፍሬና እፀ ተክል ናቸው፡፡ ሰሶች ሳር አይበሉም፡፡

 

አንድ ሴት ሰስ ከ11 እስከ 16 ኪሎ ግራም ስትመዝን፣ ወንዶቹ ከዘጠኝ እስከ 12 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ፡፡ የሁለቱም ቁመት እስከ 82 ሴንቲ ሜትር ይደርሳል፡፡ ቀንዳቸው 10 ሴንቲ ሜትር የሚደርስ ሲሆን፣ 16 ሴንቲ ሜትር የሚደርስ ቀንድ ያላቸውም አሉ፡፡

 

የእርግዝና ጊዜያቸው ሰባት ወራት ነው፡፡ አንዲት ሰስ በአንድ ጊዜ በአብዛኛው የምትወልደውም አንድ ነው፡፡ አለታማ በሆኑ ተራራማ ስፍራዎች የሚኖሩት ሰሶች፣ የአዳኞቻቸውን መምጣት የመረዳት ችሎታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ የኮሽታ ድምፅ ሲሰሙም ለጓደኞቻቸው ምልክት በመስጠት ይታወቃሉ፡

ምንጭ፡- ሪፖርተር ጋዜጣ