ማይክሮሶፍት የሰዎችን ንግግርና ስራ የሚረዳ ሶፍትዌር መስራቱን አስታወ??

ማይክሮሶፍት የሰዎችን ንግግርና ስራ የሚረዳ ሶፍትዌር መስራቱን አስታወቀ

 

ማይክሮሶፍት የሰዎችን ንግግርና ስራ የሚረዳ ሶፍትዌር መስራቱን አስታወቀ

 

ማይክሮሶፍት በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የሰዎችን ንግግር እና ስራ የሚረዳ ሶፍትዌር መስራቱን አስታውቋል።

የማክሮሶፍት አርቴፊሻል ኢንተለጀንት እና የጥናት ቡድን እንዳስታወቀው፥ “አርቴፊሻል ኢንተለጀንት” ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተሰራው ሶፍትዌር የሰዎችን ንግግር ወደ ሙሉ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችል ነው።

በሶፍትዌሩ ሙከራ የተደረገ ሲሆን፥ ሶፍትዌሩ የሰራው ስህተትም በባለሙያ ከሚሰራው ጋር ሲነፃፀር አነስኛ መሆኑ ነው የተነገረው።

የማይክሮሶፍት ኩባንያ የንግግር ተመራማሪዎች ሃላፊ ዜዶንግ ሁዋንግ፥ “ሶፍትዌሩ እና በዚህ መስክ የተሰማሩ ሰዎች የሚሰሩት ስራ ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው፤ ይህ ደግሞ ትልቅ ስኬት ነው” ብለዋል።

አሁን የተገኘው ውጤትም በበርካታ ኢንደስትሪዎች ጥቅም ላይ እንደሚውል ነው የሚጠበቀው።

የሰዎችን ንግግር የሚረዳው ሶፍትዌር በእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴያችን ውስጥ አንድ አካል ይሆናሉ የተባለ ሲሆን፥ ይህም ሶፍትዌሩ የሰዎችን ንግግር በመረዳት ወደ ሚፈልጉት ቋንቋ ለመተርጎም ስለሚረዳ ነው ተብሏል።

በማይክሮሶፍት ኩባንያ በንግግር ዙሪያ የሚደረግ ጥናት የሚያስተባብሩት ጂዮፍሬይ ዜዊግ፥ “አሁን የደረስንበት ስኬት የ20 ዓመት ድምር የስራ ውጤት ነው” ብለዋል።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk