በህይወት ያሉ የአለማችን 10 ባለ ምጡቅ አዕምሮ ባለቤቶች

በህይወት ያሉ የአለማችን 10 ባለ ምጡቅ አዕምሮ ባለቤቶች

 

በህይወት ያሉ የአለማችን 10 ባለ ምጡቅ አዕምሮ ባለቤቶች

 

በአለማችን በርካታ አስገራሚ አዕምሮ ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ የአዕምሮ ብቃታቸው (አይ ኪው) 140 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ልዩ ብቃት እና እውቀት የተላበሱ መሆናቸው ይነገራል፡፡ ከአለማችን ህዝብ 0.5 በመቶ የሚሆኑት የምጡቅ አዕምሮ ባለቤት መሆናቸውንም ነው መረጃዎች የሚያሳዩት፡፡

ከዚህ በታችም በምድራችን በህይወት ያሉ 10 ድንቅ አዕምሮ የተቸሩ ሰዎችን እንመለከታለን፡፡

 

1. ስቴፈን ሀውኪንግስ – የ70 አመቱ የእድሜ ባለፀጋ አይ ኪው 160 መሆኑ ይነገራል፡፡

በፊዚክስ እና በህዋ ሳይንስ በርካታ ስራዎችን ለአለም አበርክተዋል፡፡

ሰባት በብዛት የተሸጡ መፅሀፍትን ከማሳተማቸው ባለፈ 14 ትላልቅ ሽልማቶችንም ተረክበዋል፡፡

 

2. ኪም ኡንግ ዮንግ – የአለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ከፍተኛ የአዕምሮ ብቃት ካላቸው ሰዎች መካከል እንዲካተት አድርጎታል፡፡

በሁለት አመቱ አራት ቋንቋዎችን መናገር የቻለው ዮንግ በስምንት አመቱ ነበር በአሜሪካ እንዲማር ናሳ የጋበዘው፡፡

የአዕምሮ ብቃቱ (አይ ኪው) 210 መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

 

3. ፖል አለን – የማይክሮ ሶፍት መስራቹ ፖል አዕምሮውን ወደ ገንዘብ የቀየረ ስኬታማ ሰው መሆኑን በርካቶች ይመሰክሩለታል፡፡

ፖል 14 ነጥብ 2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ሀብት በማስመዝገብ የአለማችን 48ኛው ባለጠጋ ነው፡፡

 

4. ሪክ ሮንሰር – ሪክ እንደነ ፖል አለን በሀብት ማማ ላይ መቀመጥ ባይችልም አይ ኪዉ 192 ነው፡፡

ሮንሰር በቅርቡ ጂሚ ኪመል በሚያዘጋጀው ተወዳጅ የቴሌቪዢን ሾው ላይ በስክሪፕት ፀሃፊነት አገልግሏል፡

 

5. ጌሪ ካስፕሮቭ – በ22 አመቱ የአለም የቼዝ ሻምፒዮን መሆን የቻለው ካስፕሮቭ፥ በ2005 ራሱን ከስፖርቱ አለም አግልሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በፖለቲካው መስክ በመሳተፍ እና በመፃፍ ጊዜውን እያሳለፈም ይገኛል፡፡

አይ ኪዉ 190 የሆነው ካስፕሮቭ በሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መወዳደሩ ይታወሳል፡፡

 

6. ሰር አንድሪው ዊልስ – በ1995 በአለማችን ከባድ የሚባለውን ውስብስብ የሂሳብ ስሌት የፈቱ ሲሆን፥ በሂሳብ እና ሳይንስ ዘርፎች 15 ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል፡፡

የእኝህ የሂሳብ ሊቅ የአዕምሮ ብቃት ልክ 170 መሆኑም ተመልክቷል፡፡

 

7. ጁዲት ፖልጋር – ህፃናት ከለጋ እድሜያቸው ጀምሮ በልዩ ልዩ የትምህርት አይነቶች መሰልጠን አለባቸው ብለው በሚያምኑ አባቷ ያደገችው የ35 አመቷ ፖልጋር፥ በ15 አመቷ ቦቢ ፊሽር የተሰኘውን ታዋቂ የቼዝ ተጫዋች በመርታት ስሟን በጉልህ አፅፋለች፡፡

የፖልጋር አይኪው 170 ነው፡፡

 

8. ክርስቶፎር ሂራታ – በ16 አመቱ ናሳን የተቀላቀለው ሂራታ በ22 አመቱ በአስትሮፊዚክስ የዶክትሬት ዲግሪውን አግኝቷል፡፡

የምጡቅ አዕምሮ ባለቤት ናቸው የሚባሉት ጭምር ይቀኑበታል የተባለው ሂራታ አይኪዉ 225 ነው፡፡

 

9. ትሬንስ ታኦ – በ2 አመቱ መሰረታዊ አርቲሜቲክ መስራት ችሏል፤ በ20 አመቱ ደግሞ ከፕሪንስተን የዶክትሬት ዲግሪውን ተቀብሏል፡፡

በ13 አመቱ በአለም አቀፍ የሂሳብ ውድድር ያሸነፈው ታኦ ከ230 በላይ የምርምር ውጤቶችን አሳትሟል፡፡

የ36 አመቱ ጎልማሳ አይኪው 230 መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

 

10. ጀምስ ውድስ – በሊኒየር አልጀብራ (linear algebra) እጅግ የተካነ መሆኑ የሚነገርለት ውድስ በአሁኑ ወቅት ከትምህርት አለም የራቀ ቢሆንም ሶስት የኤሚ አዋርዶችን ተቀብሏል፡፡

የውድስ አይኪው 180 ነው፡፡

 

ምንጭ፦ fossbytes.com/