የሩዝ ውሃን ለማራኪ የፊት ገፅታ እና ፀጉር

የሩዝ ውሃን ለማራኪ የፊት ገፅታ እና ፀጉር

 

 

የሩዝ ውሃ የፀጉር ድርቀትን በማስወግድ በአንፃሩ ፀጉር የተሻለ ልስላሴ እንዲኖረው እና መተጣጠፍ እንዲችል ያደርጋል።

የሩዝ ውሃ ለፀጉራችን እና ቆዳችን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት የቅርብ ጊዜ የጥናት ውጤቶች ይፋ አድርገዋል።

የሩዝ ውሃ የፀጉር ድርቀትን በማስወግድ በአንፃሩ ፀጉር የተሻለ ልስላሴ እንዲኖረው እና መተጣጠፍ  እንዲችል ያደርጋል።

በተጨማሪም የተጎዳ ፀጉር እንዲያገግም ከመርዳት ባለፈ ፀጉራችን የተሻለ ገፅታን እንዲላበስ፣ የተሻለ የደም ዝውውር እንዲኖረንም ያግዛል ነው የተባለው ።

ለቆዳችንም ልስላሴን የሚያጎናፅፍ ሲሆን፥ በቆዳ ላይ የሚደርስን የማቃጠል አደጋ ለማቀዝቀዝ እና ለማከም፣ በፀሃይ የሚደርስን የማቃጠል ስሜትም በተመሳሳይ ለማጥፋት ይጠቅማል።

በመሆኑም በሩዝ ውሃ ፀጉርን መታጠብ የተለያየ የጤና ጠቀሜታዎችን ያስገኝልናል።

የሩዝ ውሃ በውስጡ በርካታ አንቲኦክሲዳንትስ፣ ማዕድኖች፣ ቫይታሚን ቢ ፣ ኢ ከመያዙም በላይ “ፒተራ” የተሰኘውንና የሞቱ ሴሎች እንደገና እንዲያድጉ የሚያደርገውን

ንጥረ ነገር በመያዙ ከእርጅና ጋር የሚያያዙ ምልክቶች እና ነጠብጣቦችን ከፊታችን ላይ ለማጥፋት ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው።

 

የሚያስፈልጉ ነገሮች፦

ግማሽ ኩባያ የሩዝ ውሃ፣ ነጭ፣ ቡኒ ወይም ሌላ አይነት ሩዝ ሊሆን ይችላል)

2(ሁለት) ኩባያ ውሃ

 

አዘገጃጀት፦

1.አላስፈላጊ ነገሮች ከሩዙ ላይ ለማስወገድ በመጀመሪያ ሩዙን በደንብ ይጠቡት፣

2.ከዚያም ሩዙን በጎድጓዳ ሳህን በማድረግ ሩዙ ሙሉ በሙሉ በውሃ እስኪሸፈን ውሃ ይጨምሩበት፣

3.ሩዙ ከውሃው ጋር እንዲብላላ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ይተውት፣

4.ውሃው በደንብ እስኪደፈርስ ድረስ ቀስ እያሉ ውሃውን ከሩዙ ጋር ያቀላቅሉት(ይህም በሩዙ ውስጥ ያሉ በርካታ ማዕድናት እና ቫይታሚኖች በውሃው ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል)፣

5.ከዚያም ውሃውን በሌላ ንፁህ ሳህን በመገልበጥ ለመጠቀም ዝግጁ ማድረግ ይችላሉ፣

ይህን ውሃ ቢፈልጉ ለፊትዎን አልያም ለፀጉርዎ መጠቀም ይችላሉ።

በውሃው ፊትዎን ወይም ፀጉርዎን በማሸት ከተጠቀሙ ከአንድ ወይም ሁለት ሰዓት በኋላ ይለቃለቁት።

ምንጭ፦ www.hairbuddha.net