Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

አርቲስት ሚካያ በሀይሉ

Image result for ሚካያ በሀይሉ

ሚካያ ከእናቷ ከወይዘሮ ሙሉ እመቤት ፀጋዬ እና ከአባቷ አቶ በሀይሉ ገለታ ግንቦት ፳፪ ቀን ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. አዲስ አበባ ቄራ አካባቢ ተወልዳ ያደገች ስትሆን ከአምስት ልጆች የመጀመሪያ ናት። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በቤተልሄም 1ኛ ደረጃ የህዝብ ት/ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ደግሞ በአብዮት ቅርስ ት/ቤት ተከታትላለች።[ ሚካያ ግጥም መድረስ የጀመረችው በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለች ነበረ።

 

በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. መጀመሪያ አካባቢ ድንገት በኢቲቪ የአለቤ ሾው ቀርባ ስታዜም የተመለከቷት የሙዚቃ አቀናባሪ አልያስ መልካና ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ወዲያው የአብረን እንስራ ጥያቄ አቀረቡላት።ካልተሳኩ ሙከራዎች በኋላ የመጀመሪያ አልበሟን በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. ሸማመተው በሚል መጠሪያ ለመልቀቅ በቅታለች።

 

አርቲስት ሚካያ ከአገር ውስጥ ድምፃውያን አስቴር አወቀ እና አለም ከበደ፣ ከአገር ውጭ ደግሞ ቶኒ ብራክስተን እና ትሬሲ ቻፕማን እንደ ምሳሌ ትጠቅሳለች።

 

ሚካያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ ፅሁፍ የመጀመሪያ ድግሪዋን አግኝታለች። ከሙዚቃ ስራዋ ውጭ በመምህርነት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሰራች ሲሆን የሁለተኛ ድግሪዋን በመከታተል ላይ ነበረች።[በተጨማሪም ዓላማው ለኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ መጎልበት የሆነ «ሚካያ አርት ወርክስ» የተሰኘ ድርጅት አቋቁማለች።

 

ሚካያ በገጠማት የደም ስር መቆጣት የህክምና ክትትል ስታደርግ ቆይታ ታኅሣሥ ፲፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በድንገት ህይወቷ አልፏል።የቀብር ስነ ስርዓቷ በለቡ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ ፲፮ ቀን ተፈፅሟል።ሚካያ በሀይሉ የአንዲት ሴት ልጅ እናት ነበረች።

ምንጭ፡-.wikipedia.org