እንደምንኖርባት ኘላኔት ሁሉ ¾ኛው የሰውነታችን ክፍል በውሀ የተሸፈነ ነ??

 

ውሀ (Water)

 

Image result for ውሀ (Water)

 

እንደምንኖርባት ኘላኔት ሁሉ ¾ኛው የሰውነታችን ክፍል በውሀ የተሸፈነ ነው፡፡ ውሀ ከሰውነታችን እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ጋር ከፍተኛ የሆነ ቁርኝት ያለው የእያንዳንዱን ህዋሳት ክፍሎች ለመስራትና ለማሰራት በእጅጉ ይጠቅማል፡፡ ውሀ በከባቢ አየር ውስጥ ከሚገኙ ሁለት ንጥረ ነገሮች (Hydrogen & Oxygen) ውህደት የሚፈጠር ሲሆን፤ በመሬት ላይ፣ በባህር ውስጥ እንዲሁም በአየር ላይ ለሚኖሩ ህይወት ላላቸው ነገሮች በሙሉ እጅግ አስፈላጊው ነገር ሲሆን፤ ህዋሳት ውሀን ሳያገኙ ከጥቂት ቀናት በላይ ቢቆዩ ወደ ህይወት አልባነት ለመቀየር ብዙም እንደማይቸገሩ አንኳር

 

ለመሆኑ ውሀ ምን ይጠቅማል

ሰውነት ከሚከተሉት ውስጣዊ ጉዳዮቹ በመነሳት ውሀን መፈለጉ ግድ ይለዋል፡-

• አእምሮ በሚገባ ስራውን እንዲያከናውን፤

• ከውስጣዊ የሰውነት ክፍል ውስጥ መርዛማና አላስፈላጊ ነገሮችን ለማስወገድ፤

• ስብ ምግቦችን በቀላሉ ለመፍጨት፤

• የሰውነትን የሙቀት መጠንን ለመቆጣጠር፤

• ምግብን በሚገባ ለመፍጨት፤

• የኦክሲጅን መጠን በደም ውስጥ እንዲበዛ ለማድረግ፤

• የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ለሰውነት ህዋሳት እንዲደርሱ፤

• የአካል መገጣጠሚያዎች በሚገባ እንዲንቀሳቀሱ፤

• ጠጣር እና ደረቅ ምግቦች ያላቸውን ይዘትና ድርቀት በመቀየር በፈሳሽ መልክ ወደ አንጀት እንዲገቡ ለማድረግ ይረዳል፡፡

 ውሃ ለአትሌቶች የሚሰጠው ጥቅም

 በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት በቂ ውሀ አለመጠቀም በአካል ላይ ከፍተኛ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ አካል በእንቅስቃሴ ወቅት ከሚያወጣው ላብ ጋር በተያያዘ በሚኖረው የሰውነት ክብደት መቀነስ የደምን በቱቦው ውስጥ የሚኖረውን በብዛት የመንቀሳቀስ አቅም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ እንዲህ አይነት ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ ልብ ደምን በሚፈለገው መጠን በሰውነት ውስጥ እንዲዘዋወር ለማድረግ ከፍተኛ ችግር ይገጥመዋል፡፡ ስለዚህ ውሀን ከእንቅስቃሴ በፊት፣ በእንቅስቃሴ ወቅትና ከእንቅስቃሴ በኋላ መውሰድ ደም እንደፈለገው መዘዋወር እንዲችልና በውስጥ የያዘው ንጥረ ውህድ፣ ምግብና… ወዘተ ለህዋሳት በአግባቡ እንዲደርስ፣ የውስጥ ሙቀትን ለመቆጣጠር እና ጡንቻዎች በአግባቡ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ለማስቻል፤ አእምሮ እንደሚገባው መልዕክቶችን መቀበልና ትዕዛዝ ማስተላለፍ እንዲችል ወዘተ…ይጠቅማል፡፡

ውሀን

• በየአካል ብቃት እንቅስቃሴው መሀከል በብዛት

መውሰድ፤

• ከየእንቅስቃሴዎች ሁሉ በፊት ከ2-3 ብርጭቆ መውሰድ፤

• እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ካለው የአየር ፀባይ ባነሰ ቅዝቃዜ ባለበት ቦታ ላይ ማኖር፤

• ከ60 ደቂቃዎች በላይ ለዘለቀ ጊዜ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ኃይል ሰጪ ምግቦችን የያዙ የስፖርት መጠጦችን መጠቀሙ ተገቢ ነው፡፡

• በሰዓት ከ30-60 ግራም ፈሳሽ ኃይል ሰጪ ምግቦችን መጠቀም በፍጥነት ከሚመጣ የሰውነት ድካም ከመታደጉም ባሻገር የጡንቻ ህዋሶች በብቃት ስራቸውን ማከናወን እንዲችሉ ይረዳል።

 

በጣም ብዙ አትሌቶች በማያውቁት ሁኔታ ውስጥ ሆነው እንኳን በድርቀት ይሰቃያሉ። ምክንያቱም የሰውነት የውሀ ትነት በውድድር ወቅት ይጨምራል፡፡ በተለይ ትነቱ የውድድሩ ሰዓት በረዘመ ቁጥር የአየር ፀባዩ ቀዝቃዛማ ቢሆንም እንኳን ትነቱ ይጨምራል፡፡ በአንዳንድ ሰዎች ተፈጥሮአዊ የሆነ አካላዊ ልዩነት የተነሳ በጣም በበዛ የውስጥ የውሀ ትነት ላይ ቢሆኑም የውጪው አካላቸው ላይ ምንም አይነት የገጽታ ልዩነት ላይታይባቸው ይችላል፡፡ የሰውነት የውሃ ትነት ሲያጋጥም በሰውነት ላይ የሚታዩ ለውጦች፡-

 የደረቀ አፍ

 የውሀ ጥማት

 የራስ ምታት

 ድብርት

 የጡንቻ መተሳሰር

 ከመጠን ያለፈ የሰውነት ድካም

 የሰውነት ሙቀት መጠን መጨመር

በአጠቃላይ አንድ አትሌት ያልሆነ ግን በማንኛውም ስራ ውስጥ ያለ ሰው በቀን ከሁለት እስከ ሁለት ተኩል ሊትር ውሀ መጠጣት ይኖርበታል፡፡ የአትሌት የውሀ አጠቃቀም ግን አትሌት ካልሆነው እጅግ የላቀሲሆን፤ በአትሌቶች መካከል ያለው ግን እንደሚሰሩት እንቅስቃሴ ክብደትና ቅለት እንዲሁም የጊዜ ርዝማኔ ይወሰናል፡፡ አትሌቱም ይሁን አትሌት ያልሆነው ሰው ውሀን መጠቀም የሚኖርበት ምንጊዜም ቢሆን የሰውነቱ የውሀ ክምችች እንዳይቀንስ በሚል አላማ እንጂ  ከእንቅስቃሴ በፊት ወይም በኋላ የጐደለውን ለመተካት በሚል መሆን የለበትም፡፡ አንድ አትሌት በሰውነቱ የያዘው የውሀ መጠን ብቃቱንና የጉዳቱን መጠን በሚገባ ይገልፀዋል፡፡ በሚገባ ውሀን ተጠቅሞ እንቅስቃሴውን የሚያከናውን ሰው ሳይደክም ለረጅም ጊዜ እንቅስቃሴውን ማከናወን ከመቻሉም በላይ ከድካምና ድርቀት ጋር በተያያዘ ከሚመጡ ጉዳቶች እራሱን መታደግ ይችላል፡፡ ምን ያህል ነው መጠጣት ያለብኝ የሚለውን ሀሳብ ለማግኘት፤ ከእንቅስቃሴ በፊትና በኋላ የራስን ክብደት መመዘን ተገቢ ነው፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ከእንቅስቃሴ በኋላ የሚኖረው የክብደት መቀነስ በቀጥታ ከሰውነት ውሀ ትነት ጋር ይያያዛል፡፡ ሌላው አይነት መገለጫው ደግሞ በጠዋት እና ከእንቅስቃሴ በፊት የሚደረገው የልብ ምትን /Heart beat/ መቁጠር ነው፡፡

ይኸውም የልብ ምት ከተለመደው ቁጥር በላይ ከሆነ ሰውነት ባለፈው ካደረገው ልምምድ ድካም በሚገባ አለማገገሙንና የውሀ ትነቱም በሚገባ ያልተተካ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ እርስዎ የትኛው ጋር ነዎት? አንዳንድ አትሌቶች በእንቅስቃሴ ወቅት በሚፈጠር ላብ ከውስጣቸው ያለውን ጨው (Sodium) በብዛት ያስወጣሉ፡፡ ይህ በእርስዎም ላይ እውን ከሆነ ከወትሮው ይልቅ ብዙ ውሀ መጠጣት ሊያስፈልግዎት ነው ማለት ነው። ባልተለመደ መልኩ የውስጥዎን ጨው በላብ አማካይነት በብዛት መውጣት በእንቅስቃሴው ወቅት በለበሱት ልብስ ላይ በሚቀረው ጨው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ ከዚህም ባለፈ የጡንቻ ዝለት ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ድካምም ቢሰማዎት የሰውነትዎ ጨው (Sodium) በብዛት በመውጣቱለመሆኑ አይጠራጠሩ፡፡ ስለዚህ እንዲህ አይነት ነገር በእንቅስቃሴ ወቅትም ይሁን ከእንቅስቃሴ ውጪ ከገጠመዎት የስፖርት መጠጦችን (Sportdrinks) መጠቀሙ መፍትሔ ሊሆኖት ይችላልና ይጠቀሙ፡፡

የስፖርት መጠጦች (Sport drinks) በጣም ለረጅም ጊዜና ከባድ ጫና ያላቸውን እንቅስቃሴዎችን ስናደርግ የምንጠቀማቸው መጠጦች ሲሆኑ፤ በውስጣቸው የኃይል ሰጪ ምግብና የጨው (Sodium) ንጥረ ውህዶችን ስለሚይዙ በረጅም ጊዜ እንቅስቃሴ የሚመጣ የኃይል ማጣትንና የሰውነት ጨው ትነትን በሚገባ ስለሚተኩ ሰውነት በፍጥነት እንዲያገግምና አእምሮ ስለሚቀጥለው እንቅስቃሴ ያለመሰልቸት እንዲያስብ ይረዳሉ፡፡ ትክክለኛው የስፖርት መጠጥ ከ8-10% የኃይል ሰጪ እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች ውሁድ ሲሆን፤ ስኳርን (Glucose) በከፍተኛ ሁኔታ መጠቀም ግን እጅግ የተከለከለ ነው፡፡

እርስዎ የትኛው ጋር ነዎት?

አንዳንድ አትሌቶች በእንቅስቃሴ ወቅት በሚፈጠር ላብ ከውስጣቸው ያለውን ጨው (Sodium) በብዛት ያስወጣሉ፡፡ ይህ በእርስዎም ላይ እውን ከሆነ ከወትሮው ይልቅ ብዙ ውሀ መጠጣት ሊያስፈልግዎት ነው ማለት ነው።ባልተለመደ መልኩ የውስጥዎን ጨው በላብ አማካይነት በብዛት መውጣት በእንቅስቃሴው በአጠቃላይ የሰውነት የውሀ ክምችት እንደተጠበቀ ለማቆየት ክብደታችንን፣ የውሀ መጠጫችን ምን ያህል እንደሚይዝና ምን አይነት የስፖርት መጠጦች እንደምንጠቀም ለይቶ ማወቁ ተገቢ ነው፡፡

ምንጭ፡-/media/Booklet