የሚስማማዎትና የሚያስፈልጎት ሐኪም ማግኘት

የሚስማማዎትና የሚያስፈልጎት ሐኪም ማግኘት

Stethoscope

የሚስማማዎትና የሚያስፈልጎት ሐኪም ማግኘት

 

ሐኪምዎን መምረጥ

ሁሉም ሰው ሲያመው ብቻ ሳይሆን በየጊዜው እየሄደ የሚያየው መደበኛ ሐኪም ሊኖረው ይገባል፡፡ እነዚህ ሐኪሞች ዘንድ በየጊዜው የሚሄዱ ከሆነ የተለየ ችግር ወይ በሽታ ሲገጥምዎት ሐኪሙ ስለዚያ በሽታ የተሻለ እውቀት ወዳለው የተለየ ሐኪም/ስፔሻሊስት ሊልኮት ይችላል፡፡

ሐኪሞች በሚያተኩሩበት ዘርፍ መሠረት የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ይሰጣሉ፡፡ በሠፊው ከሚታወቁ የሐኪም ዓይነቶች መካከል እነዚህ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላላ ደዌ ወይም መደበኛ ሐኪም፡-

እነዚህ ሐኪሞች በየጊዜው የሚደረጉ ጠቅላላ ምርመራዎችን ያካሂዳሉ፡፡ ለቀላል በሽታዎች እርዳታ ቢሰጡም ለከፋ እና የዘርፉ አዋቂ ወደሆኑ ሐኪሞች/ስፔሻሊስቶች መላክ ያለባቸውን በሽተኞች ይልካሉ::

የማህፀን ሐኪሞች፡-

እነዚህ ሐኪሞች በሴቶች እና በእርጉዞች ጤና ላይ ያተኩራሉ፡፡

የህፃናት ሐኪሞች፡-

እነዚህ ሐኪሞች ገና ለተወለዱና ከጉርምስና ዕድሜ ላይ ያልደረሱ ህፃናት ላይ ያተኩራሉ፡፡

የጥርስ ሐኪሞች፡-

የጠቅላላ የጥርስ ጤናን በሚመለከት ወደእነዚህ ዶክተሮች መሄድ አለብዎት፡፡

 

ምንጭ፡-Ethiopiaለውጥ