ከቁርስ ስአት በፊት አይስክሬም ቢመገቡ

ከቁርስ በፊት አይስክሬም መመገብ የአዕምሮ ብቃትን ያጎለብታል - ጥናት

 

Related image

 

ከቁርስ ስአት በፊት አይስክሬም ቢመገቡ ለአዕምሯቸው መጎልበት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ተነገረ።

በቶኪዮ ዩኒቨርሲቲ የተደረገው ጥናት እንዳመለከተው ማለዳ ከእንቅልፋችን እንደተነሳን የተወሰነ መጠን ያለው አይስክሬም መመገብ የአዕምሮ ብቃትን ለማሳደግ ይረዳል።

ቴሌግራፍ ጥናቱን ያደረጉትን ፕሮፌሰር ዮሺንሂኮ ኮጋ ጠቅሶ እንደዘገበው ጥናቱ ከዚህ ቀደም ወላጆች በተለይም ለልጆቻቸው በጠዋት አይስክሬም እንዳይሰጡ የሚመከረውን መረጃ የቀለበሰ ነው ተብሏል።

ጠቃት ከእንቅልፋቸው እንደነቁ አይስክሬም የተመገቡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በፍጥነት የመግባባት እና መረጃዎችን የማብላላት አቅማቸው አድጓል ነው የተባለው።

በጠዋት ከመኝታቸው እንደተነሱ ቀዝቃዛ ውሃ ከጠጡት ይልቅ አይስክሬም የተመገቡት አዕምሯቸው በፍጥነት ይነቃል የሚለውም ተጠቅሷል።

በ2005 በለንደን ስነ አዕምሮ (ሳይካትሪ) ተቋም የተደረገ ተመሳሳይ ጥናትም አንድ ማንኪያ አይስክሬም በውርርድ ገንዘብ አግኝተን አልያም የምንወደውን ሙዚቃ ስናዳምጥ ከሚሰማን ደስታ እኩል መልካም ስሜት ይፈጥራል።

በአጠቃላይ ጥናቱ ለአይስክሬም ወዳጆች ተጨማሪ የምስራች ነው ተብሏል።

አይስክሬም በርካታ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት የሚነገር ቢሆንም፥ አብዝተን ከተመገብነው ግን ጉዳቱ ያመዝናል።

 

ምንጭ፦ http://sacramento.cbslocal.com/