ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ (Tilahun Gessesse) - (የመዚቃው ንጉስ)

 

 

ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ (Tilahun Gessesse) - (የመዚቃው ንጉስ)

 

 

ተወዳጁ ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ መስከረም 17 ቀን 1933 ዓ.ም. ከአባቱ አቶ ገሠሠ ንጉሴ እና ከእናቱ ወ/ሮ ጌጤ ጉሩሙ አዲስ አበባ ጠመንጃ ያዥ ሰፈር ተወለደ:

: ጥላሁን የ14 ዓመት ልጅ ሳለ አያቱ ጋር ወደ ወሊሶ  በመሄድ ትምህርት መማር ጀመረ::

የጥላሁን አያት ምንም እንኳን ትምህርቱ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ቢመክሩትም ጥላሁን ግን የሀገር ፍቅር ቲያትር አርቲስቶች ትርኢት ለማሳየት ወደ ትምህርት ቤታቸው በመጡ ጊዜ ከአቶ ኢዮኤል ዮሃንስ ጋር ከተወያየ በኋላ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተቀጠረ:: ለጥቂት ጊዜ ካገለገለ በኋላ ወደ ክቡር ዘበኛ ባንድ ተቀላቅሎ ታዋቂነት ተቀዳጀ::

ጥላሁን  በብዛት የአማርኛ አልፎ አልፎ የኦሮምኛና ሱዳንኛ በመዝፈን እንዲሁም ያልዳሰሰው ሃሳብ(ስለፍቅር፣ ስለሃገር፣ ስለቤተሰብ፣ ስለፖለቲካ፣ ስለተፈጥሮ፣ ስለማህበራዊ ጉዳዮች  ወዘተ) ባለመኖሩ  የመዚቃ ንጉስ እስከመባል ደረሷል::

በመሆኑም በሱ የሂወት ዘመን የነበሩ ህጻናት ሳይቀር አውሮፕላን በሰማይ ሲያዩ “አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ በዘፈን አንደኛ ጥላሁን ገሠሠ” በማለት ይዘምሩ ነበር::

ጥላሁን ለረጅም ዘመናት ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ላበረከተው አስተዋጽዎ የክብር ዶክትሬት ከአዲስ  አበባ ዩኒቨርሲቲ እስከማግኘት የደረሰ ታላቅ ድምፃዊ ነው::

በግል ህይወቱም ጥላሁን  በተለያየ ጊዜ ወ/ሮ አሥራት አለሙ፣ ወ/ሮ ሂሩት መስፍን፣ ወ/ሮ ፊሪያል አህመድ፣ ወ/ሮ ማርታ ሲማቶስ እና ወ/ሮ ሮማን በዙ ጋር በትዳር 14 ልጆችን አፍርቷል::

ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ በ68 ዓመቱ ሚያዚያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. ከዚህ አለም በሞት አተነዋል::

ምንጭ፡-ሰዋሰዉ