በሽታን ተከላካይ የሆኑ አረንጓዴ ተክል ምግቦች

 

በሽታን ተከላካይ የሆኑ አረንጓዴ ተክል ምግቦች

 

በሽታን ተከላካይ የሆኑ አረንጓዴ ተክል ምግቦች

የአረንጓዴ ተክሎች ለጤና ጠቃሚ መሆን የማያጠራጥር ሲሆን ለዛሬ በጥቂቱ ስለተክሎቹ አይነትና ጥቅሞቻቸዉ እናካፍልዎ፡፡

ጥቅል ጎመን፦ የተለያዩ አይነት የጎመን ዝርያዎች ያሉ ሲሆን ሁሉም በቫይታሚን ኤ፣ ሲ፣ ካልሲየም እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ናቸዉ፡፡
በአዉስትራሊያ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተዉ እነዚህን አረንዴ ተክሎች መመገብ ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡

ቆስጣ፦ ቆስጣን መመገብ የጉበት፣ የአንጀት፣ የማህፀን እና የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን ከነዚህም በተጨማሪ ለጡንቻ መዳበር ጠቃሚነት አለዉ፡፡

ሠላጣ፦ ሠላጣን መመገብ ለደም ግፊት ህመምተኞችና ከፍተኛ የሠዉነት ክብደት ላላቸዉ ሠዎች የሚመከር ሲሆን የደም ዉስጥ ስር መጠንንም ይቀንሳል፡፡

ሠላጣ በዉስጡ የያዘዉ ካልሲየምና ፎስፈረስ ለአጥንት ጤናማነት ጠቃሚ ሲሆን ሴሊኒየም የሚባለዉ ንጥረ ነገር ደግሞ የሠዉነታችን ቆዳ ቶሎ እንዳረጅና የአንጀት ካንሠርን የመከላከል አቅም እንዲኖረዉ ያደርጋል፡፡

ጎመን ፦ጥቁር ጎመን በዉስጡ ቫይታሚን ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ3፣ ቢ6 ፣ሲ እና ሌሎች እንደ ፖታሲየም ፣ ካልሲየም ፣ ፎስፈረስ እና አዮዲንንም ይይዛል፡፡

የሰዉነት የበሽታ የመከላከል አቅምን የሚያጠነክርና በሽታንም የሚከላከል የተክል አይነት ነዉ፡፡

መንጭ፦ healthdigezt.com