የቲቢ በሽታ ምልክቶች

የቲቢ በሽታ


 

 

በሽታው እድሜ ፆታ ሀይማኖት ዘር ቀለም ሳይመርጥ የሚከሰት በሽታ ሲሆን ስርጭቱን አስተዋፅዖ ከሚያደርጉት ውስጥ....ህዝብ በብዛት ተፋፍኖ የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ለምሳሌ እስር ቤቶች፣ የስደተኛ ካምፓሶች፣ ትራንስፓርት ማመላለሻዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የህክምና ቦታዎች፣የቲያትርና ሲኒማ ቤቶች እንዲሁም ሌሎች በከፊል ሊጠቀሱ የሚችሉ ሲሆን በነዚህም ቦታዎች በቂ መስኮትና በር ከሌለውና በቂ አየር የማይንሸራሸር ከሆነ በቀላሉ የመተላለፍ አቅሙ ከፍተኛ ነው።

የቲቢ በሽታ በወቅቱ ከታወቀ እና መድሀኒቱን ሳይቋረጥ ለተገቢው ግዜ
በትክክል ከተወሰደ በቀላሉ ሊድን ይችላል ። መድሀኒቱን ተጀምሮ ካቋረጡት ለተላመደ ቲቢ ወይም( MDR Tb) ያጋልጣል።

በሽታው በትንፋሽና በሌሎች መንገዶች በመተላለፍ ወደሰውነታችን ውስጥ ከገባ በኋላ መራባትና መሰራጨት ይቀጥላል።ይህም ሰፋ ያለ ጊዜ ይወስድበታል።ይህም ግለሰቡ የበሽታ የመቋቋም አቅምና በሰውነት ውስጥ በገባው የባ ክቴርያ መጠን ይወሰናል።

 ምልክቶች
....... ከሁለት ሳምንት በላይ የቆየ
* ሳል
* አክታ
* ውጋት
* ከ 2 ሳምንት በላይ የቆየ ትኩሳት
* የትንፋሽ ማጠር
* የሰውነት ክብደት መቀነስ
* ከፍተኛ ላብ.......ናቸው።

 ለበሽታው በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሚሆኑት፦
• ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት፣
• አረጋዊያን፣
• በኤች. አይ. ቪ. የተያዙ ሰዎች እንዲሁም
• በአክታ ምርመራ የቲቢ በሽታ አምጪ ተሕዋስ ከተገኘባቸው ሕሙማን ጋር አብረው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው፡፡

 የቲቢ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች
• የቲቢ በሽታ በዋናነት የሚተላለፈው በሳንባ ቲቢ የተጠቃና ሕክምና ያልወሰደ በተለይም በአክታ ምርመራ የቲቢ በሽታ አምጪ ባክቴሪያ የተገኘበት ሕመምተኛ ሲስል፣ ሲያነጥስ፣ ሲነጋገር ወዘተ... የበሽታው አምጪ የሆነው ጀርም ከታማሚው ሳንባ ውስጥ በመውጣት በቀጥታ በትንፋሽ ወይም በአየር አማካይነት ወደ ሌላ ሰው የመተንፈሻ አካል ሲገባ ነው፡፡
• በሽታው አልፎ አልፎ ማይኮባክቴሪየም ቦቪስ ተብሎ በሚጠራ ጀርም
አማካኝነት በበሽታው ከተያዙ የቤት እንስሳት

 የበሽታው የማይተላለፍባቸው መንገዶች?
• በመጨባበጥ፣
• አልባሳትን በጋራ በመጠቀም፣
• መመገቢያና ማብሰያ የቤት ዕቃዎ በጋራ በመጠቀምችን አይተላለፍም።

 የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከቲቢ ሕሙማን ምን ይጠበቃል ?
• የታዘዙ መድኃኒቶችን ባለማቋረጥ ወስዶ መጨረስና በሕክምናው መጨረሻ ላይ መፈወሱን ማረጋገጥ፣
• ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ሲስሉም ሆነ ሲያስነጥሱ አፍና አፍንጫዋን
በጨርቅ ወይም በመሃረብ በመሸፈን የበሽታው አምጪ ተህዋስያን
እንዳይሠራጩ ማድረግ፣
• አክታን በየቦታው ከመትፋት ይልቅ ክዳን ባለው ዕቃ ውስጥ ተፍቶ በመቅበር ወይም በማቃጠል የቲቢ በሽታ አምጪ ተህዋስያን እንዳይሰራጩ ማድረግ፣
• የቲቢ ሕመምተኛ አብረው የሚኖሩ የቤተሰብ አባላትን፣ ሌሎች የቅርብ
ግንኙነት ያላቸው ጉረቤቶችንና የሥራ ባልደረቦችን ሁሉ እንዲመረመሩ
ማድረግ፣
• የመኝታ ቤት መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖርና የፀሐይ ብርሃንም እንዲገባ ማድረግ፤
• በተቻለ መጠን ገንቢና ተመጣጣኝ የሆነ ምግብ መመገብ፣
• ሲጋራ ከማጨስና ከአልኮል መጠጦች መራቅ።

 ከቲቢ ሕሙማን ቤተሰብ ምን ይጠበቃል ?
• የቲቢ ታካሚ የታዘዙለትን መድኃኒቶች ሳያቋርጥ በመውሰድ ከበሽታው
እንዲፈወስ ማበረታታትና መከታተል፤
• የቲቢ ሕመምተኛ አክታውን በየቦታው እንዳይተፋ ክዳን ያለው ዕቃ በማቅረብ አጠራቅሞ በተወሰነ ቦታ ማቃጠል ወይም አርቆ ቆፍሮ መቅበር፤
• የቲቢ ሕመምተኛ በሚኖርበት ቤተሰብ በተለይም አስታማሚዎችንና
ዕድሜያቸው ከስድስት ዓመት በታች የሆኑትን ሕጻናት ልጆችንና አረጋዊያንን ማስመርመር፣
• ለቲቢ ሕሙማን ፍቅር ማሳየትና በተቻለ መጠን ገንቢና ተመጣጣኝ ምግብ እንዲመገቡ ማድረግ፤
• የመኝታ ክፍል መስኮቶችን በመክፈት በቂ አየር እንዲዘዋወርና የፀሐይ
ብርሃን እንዲገባ ማድረግ፡፡

 

 ምንጭ፡- ኢትዮጤና