በጀርባችን፣ በጉልበታችን እና ዳሌያችን አካባቢ የህመም ስሜት ሲሰማን በ?

 

በጀርባችን፣ በጉልበታችን እና ዳሌያችን አካባቢ የህመም ስሜት ሲሰማን በቀላሉ ለመከላከል የሚረዱን እና በእግር ብቻ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች።

4c15acd5808a8015edffcf6b6fc4a393_L

 ሁሉም ነገር ከታች ወደ ላይ እንደሚጀመር ሁሉ፥ እግራችንም ለሰውነታችን ጤንነት ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

 ለእግራችን አስፈላጊውን እንክብካቤ ካደረግንም በጀርባችን፣ በጉልበታችን እና በዳሌያችን ላይ የሚያጋጥሙ የህመም ስሜቶችን በቀላሉ ማስወገድ እንችላለን።

 

ምን አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ይኖርብናል?

 1.በጣታችን መቆም

 እንደ ሌሎች የሰውነት ክፍላችን ሁሉ እንቅስቃሴ ከማድረጋችን በፊት እግራችንም ማሟሟቅ ያስፈልገዋል። በጣታችን መቆም ደግሞ ለእግራችን አስፈላጊ ከሆኑ የማሟሟቂያ መንገዶች አንዱ ነው።

 ይህንን ለማድረግም ከተረከዛችን ከፍ በማለት በጣታችን ለ3 ሰከንድ ያክል መቆም ይኖርብናል።

 ከዚያም ለ10 ጊዜ ያክል ደጋግመን መስራት፣ ይህንን እንቅስቃሴም በቀን ውስጥ 3 ጊዜ መደጋገም መልካም ነው።

 

2.በጣት መራመድ

 በጣት መራመድ በእግራችን ውስጥ ያሉትን ጅማቶች እና ጡንቻዎች ለማጠንከር ይረዳናል።

 ይህንን እንቅስቃሴ ለማድረግም በጣታችን በመቆም ለ20 ሰከንድ ያክል መራመድ ይመከራል።

 ተራምደን እንደ ጨረስንም ለ15 ሰከንድ ያክል ማረፍ፣ ይህንን እንቅስቃሴ 5 ጊዜ ደጋግመን መስራት።

 ለተሻለ ውጤት እንቅሰቃሴውን በቀን ከሁለት ጊዜ በላይ ባንሰራ መልካም ነው።

 

3.ቁርጭምጭሚታችንን ማንቀሳቀስ

 ቁርጭምጭሚታችን በደንብ ያልተፍታታ እና እንደፈለግን የማይታዘዝልን ከሆነ በቀላሉ ለዳሌ፣ ለጀርባ እና ለጉልበት ህመም ልንጋለጥ እንችላለን።ስለዚህም  ቁርጭምጭሚታችን በደንብ እዲፍታታ በማድረግ እንደፈለግን እንዲታዘዝልንም ማድረግ ለሰውነታችን ጤንነት እጀጉን ጠቃሚ ነው።

 ይህንን የሚረዳ እንቅስቃሴ ለማድረግም በመጀመሪያ በጀርባችን መሬት ላይ መተኛት፣ በመቀጠልም እግራችንን ከፍ በማድረግ በሁሉም አቅጣጫ የእግራችንን መገጣጠሚያን ማሽከርከር።

 በሁለቱም አቅጣጫ ለ10 ጊዜ ያክል እየደጋገምን መስራትም መልካም ነው።

 

ምንጭ፦   healthylivinghouse. Com